" ዲሽታግና ".....አዳም ወንድሜ ...!!

በአንድ ወር ውስጥ የ8.4 ሚሊዮን የተመልካች ቱጃር ሆነ ::

 

  ከአለባቸው ደሳለኝ አበሻ (ለንደን)                       

 

የሙዚቃው ኢንዱስትሪ እጅግ በጣም ፈጣን እድገት የሚታይበት፣ ተለዋዋጭና ከፍተኛ ፉክክር ያለበት በመሆኑ ብዙ ድምፃውያን የሙዚቃ ምርጫቻው እንደአሳታሚው ፍላጎት የሚለወጥበትም ጊዜ ያጋጥማቸዋል ::  በዚህ ምክኒያት ዛሬ ተወዳጅ የሆነ ሙዚቃ ቶሎ ይሰለችና፤ አሮጌ ሆኖ ሸልፍ ላይ ይቀመጣል ::  

አንድ ሙዚቃ ተወዳጅ መሆኑንና አለመሆኑን የሚወስነው  በሙዚቃው አድማጭ በመሆኑ  ሙዚቃውን  የምንመርጥበት መስፈርት ደግሞ ብዙ ነው ::  አንዳንዶቻችን የሙዚቃው ቅንብርና የድምፃዊያኑን ቅላፄ ስናደንቅ ሌሎቻችን  ደግሞ ምቱ ደስ ስላለንና  ግጥሞቹ  ወይንም የሥነ ምግባር እሴቶቻችንም  ግምት ውስጥ  አስገብተን ስለተመቸን  ከሙዚቃው  ቃና ከፍተኛ ኃይል ይልቅ  በስሜታችን ላይ ጥልቅ የሆነ ተጽዕኖ የሚያሳድረው   ጠብቅ፤ የሕይወት ግንኙነት የሚኖረው ግጥሙ ሆኖ እናገኜዋለን  :: 

ሙዚቃ በሰዎች ጤና እና ባህሪ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊኖረው ይችላል የሚለው የባለሞያዎች ምክር እንደተጠበቀ ሆኖ በአለም አቀፍ 

 ተወዳጅ እንዲሆንና በብዛት  እንዲደመጥ እንዲሸጥ ምክኒያት የሚሆነው ግን የወጣቱ  ተሳትፎ ነው ::  በተለይ የግጥምና የዜማ ደራሲዎችም ቢሆኑ በበኩላችው  የሰዎችን ስሜት የሚኮረኩሩ ማለትም በተስፋቸው፣ በሚያልሙት ነገርና በውስጣዊ ስሜታቸው ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ስንኞችን ለማዘጋጀት ስለሚጥሩ ወጣቱ ለሙዚቃው ኢንዱስትሪ ማደግ ትልቅ አስተዎፅዎ አድርጏል ::

ሆኖም ግን በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት ማግኘት የሚችሉና  እድሜ ጠገብ ሆነው የሚዘልቁ በጣም ጥቂት ድምፃዊያን ካልሆኑ በቀር አብዛኛዎቹ ሞያቸውን እርግፍ አርገው  በመተው መድረኩን ጥለው በመውጣት በተለያየ ሞያ ተሰማርተው ይገኛሉ :: ::

 እንደምን አላችሁልኝ ውድ የፌስ ቡክ ወዳጆቼ 

ለዛሬው ይዤላችሁ የምቀርበው በዩቲዩብ ተለቆ በአንድ ወር እድሜ ውስጥ የ8.4 ተመልካች ቱጃር ስለሆነው  የድምፃዊ ታሪኩ ዲሽታግና

የኦሪስ ብሔረሰብ ዘፈን ነው ::

በቅድሚያ የሙዚቃ ግጥሞቹ ሲዘጋጁ የሰውን ልጅ ስሜትና የልብ ትርታ ለመግዛት በፍጥነትና  በዝግመት እየጠበቁ በምርጥ የሙዚቃ ቃናን ተከሽነው አዕምሮአችንን ጠልቀው ለመንካት ለማዝናናት ኃይል እንዲኖራቸው ተደርገው ስለተዘጋጁ አይረሴነት ይዘት አላቸው ::

በግጥሙ ስንኝና በሙዚቃው ቅንብር ውስጥ የተውኔት ጥበብ፣ይታይበታል ::  

 

ዲሽታግና የአሪ ብሔረሰብ አዲስ ዓመት ወይም ዘመን መለወጫ ነው። ዲሽታግና አብረን እንብላ፣ አብረን እንጠጣ፣ የተጣሉትን እናስታርቅ ፣ ለሌላቸው እንስጥ፣ እንደጋገፍ ማለት ነው።

  ዲሽታግና  አድማጩን በመወክልና የስንኙ ተዋናይ እንድንሆን የሚደርግ  ሲሆን በሙዚቃው ምት እንቅስቃሴ መላውን የሰውነት አካል እያፍታታ ሲደመጥ ደስ በተሰኙና ቀለል ባሉ ግጥሞቹ እኛንም ሌሎቻችንንም እርስ በእርስ እንድንተያይ  የታሪኩ ባለቤቶች ሁላችንም በማድረግ የተሸሸጉ በርከታ ማንነትን ወደ አንድነት በማምጣት ዘፈኑን አጏጊ አድርጎ እንድንቀላቀልና እራሳችንን እንድንጠይቅ ልብ እንድንገዛ ጭምር በማድረግ ያሳትፋል :': 

በሌላ አኳያ ዘፈኑ ከሙዚቃው ጋር ተስማምቶ ድምፃዊ ታሪኩ ጋንኪሲ ሊገልፀው  የፈለገውን ፍሬ ነገር   በሚገርም ጥበብ  ለሁሉም የሰው ዘር  እንደሚጥቅም አድርጎ በመልዕክትነቱ  ለማስተላለፍ ችሏል :: 

 በነገራችን ላይ ሙዚቃ በቴክኒክ ቅንብር የዳበረ መሆን ስለሚገባው ድምፃዊው የሚጠበቅበትን ድርሻ በፈጣራው ውስጥ እነዚህን ቴክኒኮች ተጠቅሞ መልዕክቱን አግዝፎና አጉልቶ ሊያስደምጠን ሲችል ብቻ ነውየተዋጣለት ነው የምንለው ::

 

ዲሽታግና  ስንኙቹ ባይታወር የሚያደርጉ ሳይሆን በምሳሌነት የተጠቀሰው አዳም ወንድሜ ሕይዋን እህቴ  የሰውን ልጅ አፈጣጠር    ተመርኮዞው በሀይማኖትና በዘር ለሚናከስ ማሕበረሰብ በጥልቀት እራሱን እንዲፈትሽ አግዝፈው የሚያስገነዝቡ የፈጠራ ተልእኳቸውን  የሚያሳዩ ናቸው    :: 

ዲሽታግና  ከዚህም በላቀ ደረጃ አንድን የ10 አመት የጎዳና ታዳጊ ወጣት አቡሽን  ከአደንዛዥ ሱስ ያላቀቀ  ከእውነተኛ የሰው ልጅ ውስጣዊ ስሜት ጋር የጠበቀ ዝምድና ያስገነዘበና የተፈጥሮን ዳኝነት የእውኑን አለም እውነታ በገሀድ ያሳየ በመሆኑ የሕይወት  ሚስጥራዊ ተልዕኮ አለው ማለት ይቻላል :: 

ዲሽታግና በችግርና በሀዘን የተቆራመደን ታዳጊ ከትካዜና ከቀዘቀዘ ሕይወት በጥልቀት ገብቶ  የብቸኝነት ጥላውን ገፎ ዝምታን አሰብሮ

በሞቀ ፈገግታ ሽመሉን አስጨብጦ ዳንኬራ ማስመታት ብቻ ሳይሆን ከጎዳና አንስቶ ሕይወቱን ቀይሮታል :: 

ዲሽታግና በዚህና በብዙ.ምክኒያት ድምጻዊው ታሪኩ ጋንኪሲ

ማንነትን ያሳየንና የእሱነቱ መገለጫ  ውስጣዊ የፈጠራ ባሕሪውን ጭምር  ሁለተናዊ አስተዋይነቱን አጉልቶ ሊያስነብበን ችሏል  ::

በበኩሌ የትያትር ጥበብንና የፊልምን ቴክኒዎለጂ አድናቂ እንጅ  ገፋ በሙዚቃ ስራዎችን ላይ ስለማልሳተፍ በግርድፉ ካልሆነ በቀር ብዙም የጠለቀ እውቀት የለኝም ::

ቢሆንም  በአንድ ወር ውስጥ ከ8..4  ሚሊየን በላይ ተመልካቾችን ያገኘውን ዲሽታግና አለማድነቅ አይቻልም ::

ቀደም ብየ ከመግቢያዬ ላይ እንደገለፅኩላችሁ ድምፃዊው ታሪኩ ጋንኪሲ በቀላል ስነግጥም በውስጡ የፀነሰውን ሐሳብ ይዞ ለቃላቱ ሳይጨነቅ በዜይባዊ አነጋገሮች አዚሞ ሕብረ ብሔራዊ ቀለም ሰቶታል :: የመጨረሻውን እፁብ፣ድንቅ ከሚሰኙ የይዘትና ቅርፅ ደረጃ ላይ ለመድረስ ማቋረጥ ያለበትን ውስብስብ ሒደት አልፎ ድምፃዊ ታሪኩ በአንድ ነጠላ ዘፈን አንድ የሙዚቃ ሐውልት ቀርፆ አቁሞ አሳይቶናል  ::

ለዛሬው የጎዳናውን አቡሽና  ድምጻዊው ታሪኩ ጋንኪሲ መልካም እድል የተመኜሁ ዝግጅቴን በዚሁ አበቃሁ :: የተረፈውን እናንተ ጨምሩበት 

 በሌላ ዝግጅት እስክንገኝ ፣ እድሜ ይስጠን ጤና ይስጠን  እሩቅ ካሉት ቅርብም ካሉት ቸር ያሰማን  ደቡብ ፣ ሰሜን ፣ ምዕራብ ፣ ምስራቅ ፣ በቸር አድሮ በቸር ይንጋ

 

አለባቸው ደሳለኝ አበሻ (ለንደን)

Sign in or sign up to post comments.
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular