ቤተ ክርስቲያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ላመጡት እርቅና ሰላም ልዩ ሽልማት አበረከተች

ቤተ ክርስቲያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ላመጡት እርቅና ሰላም ልዩ ሽልማት አበረከተች

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ላመጡት ሰላምና እርቅ ልዩ ሽልማት አበረከተች።

Image may contain: 4 people, people smiling, people standing

ቤተ ክርስቲያኗ ልዩ ሽልማቱን ያበረከተችው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ብሎም በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ሰላም እንዲመጣ አድርገዋል በሚል ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሽልማቱን በተረከቡበት ወቅትም፥ ሽልማቱ ያለእረፍት ይህ ነገር እንዲመጣ ሲታገሉ ለነበሩ እና ይህ ለውጥ እንዲመጣ ሲፀልዩ የነበሩትን በሙሉ የሚገባ ነው ማለታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ልዩ ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል።

በሙለታ መንገሻ

Source: Fana Broadcasting

Sign in or sign up to post comments.
Be the first to comment

Related Articles

 • ብርሀን ዘ ኢትዮጵያ ........!! ጣይቱ ብጡል (እቴጌ )
  ብርሀን ዘ ኢትዮጵያ ........!! ጣይቱ ብጡል (እቴጌ ) እንደምን አላችሁልኝ ውድ የፌስ ቡክ ወዳጆቼ :: ለዛሬው አብሪያችሁ የምቆየው ፣ የግዙፍ ሰብዕና ፣ባለቤት በኢትዮጵያ ፣ሴቶች ታሪክ ፣ ውስጥ...
 • " የግዜና የዘመን ተወቃሽ ትውልድ እንዳንሆን !! "
  የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ በምሐበራዊ ሚዲያያዎች ተከታትየው ነበር :: በተለይ በመግለጫቸውም ትኩረት ባደረኩበትን ብቻ ላይ የግል...
 • የመጨረሻዋ ስዓት !!
  " የመጨረሻዋ ስዓት !! " " ከእያንዳንዱ ብርሀን ጀርባ ጨለማ እንዳለ አስተውል፡፡ ያለህበት ብርሀን ዘላቂ ይሆንልህ ዘንድ መልካም ነገሮችን ብቻ አድርግ፡፡ ክፋት ካከልክበት ከጨለማው ስር ትወድቅና...
 • " ዲሽታግና ".....አዳም ወንድሜ ...!!
  በአንድ ወር ውስጥ የ8.4 ሚሊዮን የተመልካች ቱጃር ሆነ :: ከአለባቸው ደሳለኝ አበሻ (ለንደን) የሙዚቃው ኢንዱስትሪ እጅግ በጣም ፈጣን እድገት የሚታይበት፣ ተለዋዋጭና ከፍተኛ...

Latest Articles

Most Popular