Featured

Ethiopian Music : - Mesfin Bekele መስፍን በቀለ "ሚስጥር ነው" New Ethiopian Music 2020(Official Video)

370 Views
Published
Ethiopian Music : - Mesfin Bekele (Mister New) መስፍን በቀለ "ሚስጥር ነው" New Ethiopian Music 2020(Official Video)
:- ከምነው ሸዋ ቲዩብ...

ዝነኛው እና ተወዳጁ ድምፃዊ መስፍን በቀለ ከዚህ ቀደም በሁለት ሙሉ የሙዚቃ አልበም እና በስኬታማ ሀገራዊ ድንቅ ስራዎቹ ብሎም በተለያዩ ነጠላ ዜማዎች ሰምተን የወደድነው አይትን የመሰከርንልተ ተወዳጅ ስራዎችን ሲያቀርብልን እንደነበር ምስክራችን እናተው የጥበብ አክባሪዎች እንደሆናቹ ምንም ጥርጥር የለንም::
ስለዚህ ዛሬም እንደትናቱ ሁሉ (ሚስጥር ነው) በሚል መጠሪያ ነጠላ ዜማ ከብዙ ድካም በኃላ በከፍታ ይዞላቹሁ ብቅ ብሏል::
ይህ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ አዲስ ስራ እጅግ በርካታ ባለሞያዎችን ያሳተፈ ሲሆን የመጀመሪያ ቀረፃውን በዋሽንግተን ዲሲ በመስፍን ፊልም ፖሮዳክሽን ካሜራ ቀረፃ አማካኝነት ብዛት ያላቸውን ሰዎች በማሳተፍ ሲከናወን : ብሎም በሎንደን ከተማ በተደረገው የቪዲዬ ቀረፅ (በኪሮሽ) ፊልም ፖሮዳክሽን አማካኝነት ካሜራ ቀረፃ ተከናውኖ ሲያበቃ : ዋናው እና ትልቁን የአንበሳውን ድርሻ በመውሰድ ዳኒኪራ የኪነጥበብ ዳንስ ጉሩፖ የውዝዋዜውን እና ሙሉ ዝግጅቱን ባማረና በደመቀ ሁኔታ : በዳኒኤል ዱላ ዳሬክቲንግ በመመራት እጅግ በርካታ የሙያ ጥበብኞችን በማሳተፍ ደረጃው በጠበቀ ሁኔታ ወደናተ አምሮ እንዲደርስ በአግባቡ የተከወነ ስራ ነው::
ሌላኛው እና ከሌሎቹ እንደ አንደኛው የአንበሳውን ድርሻ ከሚወስደው ዋነኛውና ትልቁ ደሞ የሙዚቃው አቀናባሪ አሌክስ ይለፍ ነው::
ይሄ ወጣት እና ተወዳጅ ባለሙያ በርካታ ተጨማሪ መሳሪያ ተጫዎቾችን በማሳተፍ እዚህ ሙዚቃ ላይ ዜማን ከከሙዚቃ ጋር አዋህዶ ከሚጣፍጥ ቅንብር ጋር ህይወት የዘራበት ጉራማይሌ ልጅ ነው::
ታድያ ይሄ ሁሉ ነገር ግጥጥሞሹ ምን ይሆን በማለት ሚስጥሩን በመረዳት ብሎም ለእናተ ለማሳወቅ በከፍተኛ ፍላጎት ወጪ በማውጣት ወስነን የአርቲስቶቻችን ነፅብራቅ የሆነው ምነው ሸዋ ቲዩብ ይሄን ትልቅ ስራ ለሀገር ወዳድ ኢትዮጵያንዊን የጥበብ አፍቃሪዎች : እና ለቻናላችን ቤተሰቦች ይደርስ ዘንድ ስናቀርብ በታላቅ ኩራት ነው::
ምነው ሸዋ ኢንተርቴመንት

"ሚስጥር ነው"
የአንድነታችን ሚስጥሩ ኢትዬጲያዊነት የአሸናፊነት ምልክት ረቂቅ ሚስጥር ነው:: ሀገራችን ከውጪ የመጣባትን ወረራ በታሪኳ አንድም ጊዜ ሳትሸነፍ ለሀያላን ሀገሮች ሳትንበረከክ በጀግኖች ልጆቾ መሰዋትነት እንደወርቅ በእሳት ተፈትና ልዕልናዋን: ያስከበረቸ ታፍራና ተከብራ የኖረች ወደፊትም የምትኖር ታላቅ ሚስጥረ እግዚአብሔር ያላት: ኢትዮጵያ ቀደምት ምድረ ገነት ሀገር ናት::
ማስታወሻ
ይህ የጥበብ ስራዬ ማስታወሻነቱ ኢትዮጵያችንን በደም እና በአጥንታቸው አስከብረው እነሱ መሰዋት በመሆን በክብር ላቆዩልን ጀግኖች እባቶቻችን እና አይቶቻችን እንዲሁም በጀግነታቸው ወደር ለማይገኝላቸው በየዘመናቸው ገድል ለፈፀሙ አሁንም በህይወት ለሚገኙ ኩራቶቻችን (የካራማራው) ፈርጦች እስከ ዛሬ በጀግነታቸው ሳይዘመርላቸው ለኖሩ እንደ አሊ በርኪ ደፋር እና ቆራጥ ጀግና ልጆቾዋ አንዲሁም ለአባቴ መቶ አለቃ በቀለ ፉርጋሳ የክብር ማስታወሻዬ ይሁንልኝ::
መስፍን በቀለ
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር
Sign in or sign up to post comments.
Be the first to comment