ብርሀን ዘ ኢትዮጵያ ........!! ጣይቱ ብጡል (እቴጌ )

ብርሀን ዘ ኢትዮጵያ ........!! ጣይቱ ብጡል (እቴጌ )

እንደምን አላችሁልኝ ውድ የፌስ ቡክ ወዳጆቼ :: ለዛሬው አብሪያችሁ የምቆየው ፣ የግዙፍ ሰብዕና ፣ባለቤት በኢትዮጵያ ፣ሴቶች ታሪክ ፣ ውስጥ እንደክዋክብት ብርሐን ታሪካቸውን በአለም የነፃነት ታሪክ መዝገብ ላይ ፣በወርቅ ቀለም ፣ ፅፈው ይችን መከረኛ አለም ከተሰናበቱ አንድ መቶ አመት፣ ስለሞላቸው ፣ ታሪከ ደምም እቴጌ፣ ጣይቱ ብጡል ብርሐን ዘኢትዮጵያን ፣ የህይወት ጉዞ አስቃኛችዃለሁ :: በጥቁሩ ዓለም ውስጥ በነፃነቷ ኮርታ ለሌሎቹ ምሳሌ የምትሆን ኢትዮጵያን ፣ ከምንይልክ ጋር ተረክበው ፣ ሐገራቸውን በጦርነተም ፣ በፓለቲካውም ፣ በመንፈሳዊ ጠንክራ፣ ለአለም እንድትታይ እስከ እለተሞታቸው ድረስ የደከሙት ብርሀን ዘኢትዮጵያ ጣይቱ ብጡል ናቸው :: 
ብርሐን ዘኢትዮጵያ ጣይቱ ፣ በጦርነትም ወቅት ፣ ለአርበኛው ሁሉ ማነቃቂያ ለወዶቹም፣ ለሴቶቹም፣ ፅናትና ተምሳሌት ሲሆኑ ፣ አገር ና ታሪካቸውን ከቅኝ አገዛዝ ወራሪ ፣ የተከላከሉ ፣ የውጫሌን ውል ተፀይፈው ኢትዮጵያ አትቀበልም በማለት ፣ በአቋማቸው ፀንተው አለምን ያስደመውን ፣ ውሳኔ በማስተላለፍ የአድዋውን ጦርነት ከምንይልክ ጋር የመሩ ፣ የጦር ፊታውውራሪ ጣይቱ ብጡል ብርሐን ዘኢትዮጵያ ናቸው ::
እቴጌ ጣይቱ ብጡል ፣ በነሐሴ አስራ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ሰላሳ ሁለት ፣ በጎንደር ክፍለ ሐገር በደብረ ታቦር ከተማ ተወለዱ :: በደብረ ታቦር እየሱስ ቤተክርስቲያን ክርስትና ተነሱ ::ብላቴን ጌታ ህሩይ በአሳተሙት መፃፋቸው ላይ 
“ጣይቱ በምትባል ሴት የኢትዮጵያ መንግስት ታላቅ ይሆናል እየተባለ ሲነገር ይኖር ነበርና ከአፄ ምኒልክ አስቀድሞ የነበሩ አንዳንድ ነገሥታት ስሟ ጣይቱ የምትባል ሴት እየፈለጉ ማግባት ጀምረው ነበር። ነግር ግን ጊዜው አልደረሰም ነበርና አልሆነላቸውም። ዘመኑ በደረሰ ጊዜ ግን አፄ ምኒልክ እቴጌ ጣይቱን አገቡ። " ይላሉ :: ኢትዮጵያን ታላቅ ለማድረግ ትእንቢት ሲነገር ላቸው የነበሩት ጣይቱ ብጡል ጊዜው በደረሰ ግዜ ዳግማዊ ምንይልክ 
የንጉሰነገስት ዘውድ ጭነው ንጉሰነገስት ዘኢትዮጵያ ሲባሉ ፣ በሶስተኛው ቀን ጥቅምት ሀያ ሰባት 1882 ሐምሳ አንድ ጊዜ መድፍና ለሰባት ስአት የፈጀ ተኩስ እየተኮሰላቸው የተመሰገኑት ቆንጆዋ የደስ ደስ ያላቸው ደማሟ ብልህና ፣ ጀግናዋ የኢትዮጵያን የዘመናዊ አዋላጅ ጣይቱ ብጡል በቅዱስ ቁርባን ምንይልክን አግብተው እቴጌ ጣይቱ ብርሐን ዘኢትዮጵያ የሚል የክብር ስም ተሰጣቸው :: በዚሁ ስም የክብር ምሐተም ተቀረፀላቸው ::
ከምንይልክ የአራት አመት ታላቅ የነበሩት ጣይቱ ብጡል የተወለዱት በንሐሴ አስራ ሁለት ሲሆን ምን ይልክም የተወለዱት ነሀሴ አስራ ሁለት ነው
ጣይቱ ብጡል በኢትዮጵያ ፓለቲካ አስተዳደር አንፃር በነበራቸው ችሎታ በታሪክ ተመራማሪዎች ዘንድ ተደናቂነትን ሲያተርፍላቸው 
በየግዜው ይነሱ በነበሩት የሐገር ጉዳዮች ላይ ይይዙት የነበረው አቋም ፣ ይሰጡት የነበረው ውሳኔ ፣ ያቀርቡት የነበረው ብልሐት፣ ያስተላልፉት የነበረው ትዕዛዝ ፣ ሙሉ በሙሉ የሚኒሊክን ተቀባይነት ያገኜ ነበረ :: እነዚህን ታሪካዊ የህይወት ፣ ጉዞ ሂደቶች በፖለቲካው በወታደራዊ ፣ ማህበራዊ ኑሮ ውስጥ፣ ከፍተኛ ብሩህ ሚና ለመጫወት ያስቻላቸው ፣ ብዙ ሁኔታዎች ነበሩ ::ከዚያም ባለፈ ከፍተኛ የድፕሎማትነት ችሎታ የነበራቸው አስተዋይነት ታጋሽነት ያጣመሩ ናቸው ::
እቴጌ ጣይቱ ብርሐን ፣ ዛሬ በኢትዮጵያ ተደናቂነትን ፣ ካላቸው ታሪካዊ ቅርሶች ውስጥ አንዱ ፣ የሆነውን ስመ ጥሩውን ፣ የእንጦጦ ማሪያም ቤተክርስቲያንን ፣ ያስገነቡ ሲሆን በጠቅላላው ፣ አስራ ስድስት አብያተ ቤተክርስቲያንን ፣ ማሳነፃቸውን በተአምረ ማርያም እና በወንጌሉ ፣ ዳር ተፅፎላቸው ይገኛል :: ከዚህ በተጨማሪም የአፍሪካን መዲና ፣ የሆነችውን ፣ አዲስ አበባ ከተማን የቆረቆሩ እውቅ ምሐንዲስ ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያን ዘመናዊ ለማድረግ በተደረገው ጥረት ሁሉ ፣ የምንይልክ ቀኝ እጅ ሆነው ፣ ጥርጊያውን አፅድተው አውራ ጎዳናውን የከፈቱት ብርሐን ዘኢትዮጵያ ጣይቱ ብጡል ናቸው :: በነገራችን ላይ ጣይቱ ብጡል ያልተሳተፉበት ልማት አልነበረም :: ስልኩም ባቡሩም ኤሌትሪኩም ፊልሙም ቧንቧ ፣ ውሐውም መኪናውም ፣ ት/ቤቱም ፣ ሆስፒታሉም ፣ ሆቴሉም ሆነ መንገድ መገንባትና ፣ ዘመናዊ መሆን የጀመረው ፣ በጣይቱና ፣ በምንይልክ ግዜ ነው ;: በዚህ ባለንበት ዘመን ሁነን ከቀደምት ጀግኖቻችን ታሪክ ገድል ስንፈትሽ ፣ በኢትዮጵያ ሴቶች ታሪክ ውስጥ ፣ ኢትዮጵያን ተረክቦ ለማቆም ፣ በከተፈለው መስዋዕትነት ፣ ጭምር ትልቁን ስፍራ የያዙት ፣ የአድዋዋ ጀግና ፣ ጣይቱ ብጡል ብርሐን ዘኢትዮጵያ አንዷ ናቸው ::
ጣይቱ ብጡል ብርሐን ፣ ዘኢትዮጵያ ፣ የኢትዮጵያ ፣ልጆች በባእድ አገዛዝ ፣ ስር ተንበርክከው ፣ባርነትን እንዳይቀበሉና ፣ ሐገራቸውን እንዳይነጠቁ ፣ ወረራን እንዲመክቱና ፣ ሉአላዊ ሐገራቸውን እንዲጠብቁ ፣ ዳርደንበራቸውን እንዲያስከብሩና ፣ ውስብስብ የነበረውን ጦርነት ፣ በአሸናፊነት እንዲወጡ ፣ ሶስት ሺህ እግረኛ ጦር ስድስት ሽህ ፈረሰኛ ጦር እየመሩ ታቦት አስይዘው የአድዋውን ጦርነቱን በነፍጥም ፣ በመንፈስም የመሩ ናቸው :: ከዚህ አኳያ የኛ ትውልድ ማወቅ የሚገባን ፣ ቁም ነገር ቢኖር ፣ ያለ እምዬ ምንይልክ ያለ ጣይቱ ብጡል ፣ ያለ ባልቻ አባ ነፍሶ ፣ ያለ አሉላ አባ ነጋ ፣
ያለ ገበየሁ ጎራ ፣ ወ..ዘ..ተ.የአድዋውን ጦርነት ማሸነፍ እንደማይቻል እንኳን እኛ ጠላቶቻችን መስክረዋል :: እኛ ባልተፈጠርንበት ዘመን እነዚህ የኢትዮጵያ መከታ ነበሩ :: ታዲያ የነዚህን ጀግኖችን ታሪክ ስንደብቅ ፣ ኢትዮጵያንን እየደብቅናት ነው :: የነ ጣይቱ ብጡል ታሪክ ስናጠፋ ፣ ኢትዮጵያን እያጠፋናት ነው :: የነእዚህ ጀግኖች ሐውልት እንዳይቆም ስንከለክል ፣ ከሐገር ጠላቶች ከነ ሞሶለኒ ፣ ብምን ልንሻል እንችላለን ::
ኢትዮጵያን ለማቆየት ተከታታይ የመስዋእትነት ፣ ውርስ አለ :: በየዘመኑ የሚነሱብን ጠላቶች የየዘመኑ ትውልድ አንገት ለአንገት እየተናነቀ ወድቋል :: የመሞት ውርስ ሳይቀር ተረካክበናል:: ታዲያ እኛ መሞት ቢያቅተን ለኢትዮጵያ ክብር የሞቱላትን ፣ ጀግኖቻችንን ታሪክ ለትውልድ እንዳይተላለፍ ፣ ቅርስ አልባ እንድንሆን የሚከለክሉን ፣ እነማን ናቸው :: እንደኔ እንደኔ ለነገ ቅርስ ለማቆም.ፍቃደኞች ካልሆን ዛሬ ጀግና አንፈጥርም :: ይህ ትውልድ ክፉ ትውልድ መሆን የለበትም:: ካለንበት የቁም እንቅልፍ ልንባንን ይገባናል :: ኢትዮጵያ ዊ የሚለውን ፣ የዜግነት መለያ የምንቀበለው ፣ በኩራትና በራስ የመተማመን መንፈስ ፣ መሆን አለበት ::
አሁን አዲስ ራኤ አንስተን በመደመር ፣ ለሁላችንም የምትበቃ ሐገር እንደ አድዋ ጀግኖች እጅ ለእጅ ተያይዘን ፣ ኢትዮጵያ መገንባት ሲገባን ዛሬም እንደትናንትናው የዘር ፣ የቋንቋ ቡቲቶ ፣ እየጎተትን ከአንድነታችን ፣ይልቅ የምንለያይበትን ፣ ክር ለመበጠስ እንደረደራለን :: ይህ ትውልድ ኢትዮጵያውነቱ ለማክሰም የታሪክ እምነቱን የባህል እሴቱን ለማውደም ሞራሉን ሐገራዊ ስሜቱን ወገናዊ ፍቅሩን የጋራ መተሳሰሩን፣ለማላላት የኢትዮጵያ ጠላቶች ተጠቅመውበታል :: ከአሁን በዃላ ግን በላያችን ላይ የሚጎሰምብን የመንጋ ፓለቲከኞች የሞት ነጋሪት አናዳምጥም :: ጣይቱ ብጡል ብርሐን ዘኢትዮጵያ ፣ ጠላት እንኳን ሊደመስሰው ፣ ያልቻለውንና የማይችለውን ፣ የዘመናዊነት ስም ፣ እና የጀግንነት ዝና ለሐገራቸው አትርፈዋል :: በርህራሔና በልግስና ፣ እጅግ የተወደዱ እቴጌ ሲሆኑ በቆሙለት አላማ ፣ የሚፈታተን ጉዳይ ፣ በሚፉጠርበት ጊዜ አንደበተ ርእቱ በመሆናቸው ፣ ቆራጥ አቋም ያላቸው ፣ የማይወላውሉ :: ተግባራቸው : ውሳኒያቸውን : ግልፅ አድርገው : ማስቀመጥ የሚወዱ በመሆናቸው ከምንይልክ ጋር ተደጋግፈው ፣ በጦርም በሰላምም ጊዜ እኩል በመኖር ፣ እቴጌ የእህትና የሚስት ፣ የንግስትነት ሚናቸውን ተወተዋል :: የሆነ ሆኖ እስከአሁን ፣ ድረስ የእቴጌ ጣይቱ ብጡል ባህሪና ጀግንነት በትክክል ፣ የሚወክል ቃል በእኔም ፣በታሪክ ተመራማሪዎችም አልተገኜላቸውም ::
ሐይመኖተኛዋ በገና ደርዳሪዋ ፣ የሐገራቸውን ደህንነት ምንግዜም የሚስቀድሙት ፣ አስተዋይና ቆራጧ ፣ ብርሐን ዘኢትዮጵያ ፣ የካቲት 4 ቀን 1910 ሰኞ በመንፈቀ ለሊት ፣ የስም ማስጠሪያ የሚሆን ከአብራካቸው አንድ ልጅ እኳን ፣ ሳይተኩ ምሐኗ ብርሐን ዘኢትዮጵያ ይህችን መከረኛ አለም ተሰናብቱ :: አስከሬናቸውም በወርቅ ሐረግ በተከበበ የእንጨት ሳጥን ውስጥ ፣ ከገባ በዃላ ፣ በመንበረ ፀሐይ እንጦጦ ማርያም ፣ ቤት ውስጥ በታላቅ ክብር አረፈ::
ሆኖም ግን ፣ ንግስት ዘውዲቱ በታህሳስ 1920 የአፄ ምንይልክን አፅም ፣ ከቤተ መንግስት አስወጥተው ፣ በባእታ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሲያኖሩ 
የእቴጌን የንዛዜ ቃል አክብረው ፣ የብርሐን ዘኢትዮጵያ ጣይቱ ብጡል አፅም ከእንጦጦ ማርያም ወርዶ ፣ በባእተ ቤተክርስቲያን ከታላቁ የአድዋው ጦር መሪ ፣ ከኢትዮጵያ ንጉሰነገስት ፣ ከዳግማዊ ምንይልክ ጎን ፣ በባእታ ቤተክርስቲያን ፣ በክብር አርፎ ይገኛል ::
ጣይቱ ብጡል ዘኢትዮጵያ ዝንት አለም ፣ ከመቃብር በላይ እንደተሰቀለ ፋኖስ ፣ ከሐጉር ሐጉር ፣ እያንፀባረቀ የአድዋውን ፣ ገድል እየመሰከረ፣ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ፣ የአፍሪካ የነፃነት ምልክት ሆኖ ፣ ለዘላለም የሚኖር ታሪክ ሰርተው ቢያልፉም ፣ እስከ አሁን ድረስ ስማቸውን የሚያስጠራ ፣ አንድም ፣ ሐውልት ሳይሰራላቸው በመቅረቱ፣ በታሪክ ተመራማሪዎችና ፣ በቅርስ ተቆርቋሪዎች ፣
በኩል ከፍተኛ ቅሬታን ቢቀሰቅስም ፣ አንፀባራቂው የአድዋው ታሪክ እንዳይነሳና የአባቶቻችን ታሪክ ፣ ለትውልድ እንዳይተላለፍ ፣ በማይፈልጉ፣ኢትዮጵያን በሚጠሉ ክፉ ሰዎች ምክኒያት እስከ አሁን ድረስ ለክብራቸው የሚመጥን ሐውልት አልቆመላቸውም :: ሆኖም ግን ይዋል ይደር እንጅ ኢትዮጵያን በክፉ የሚያይ ሁሉ መጨረሻውን ታሪክ ቁጭ ብለን እያሳየን ስለሆነ ዋጋቸውን እንደስራቸው እንደሚቀበሉ እርግጠኛ ብሆንም ፣ አንድ ቀን ግን፣ እውነተኛ የኢትዮጵያ ልጆች ተባብረው ፣ ለምሐኗ የአድዋ ጀግና ሐውልቷን እንደሚቆሙላት ህልም አለኝ ::
ለዛሬው ግን ይህን ታሪክ ስፅፍ እንደከዚህ ቀደሙ ደስ ብሎኝ ሙሉ የመንፈስ ኩራት እየተሰማኝ ሳይሆን በብዕሬ ላይ በሚፈሰው ቀለም ሳይሆን በደሜ የፃፍኩት ያህል ጥቃት እያመመኝና እንባ እየተናነቀኝ ነበር የፃፍኩት !!! ::
ለዛሬው በዚሁ አበቃሁ በሌላ ዝግጅት እስክንገናኝ ቸር ይግጠመን ::
አለባቸው ደሳለኝ አበሻ ( ለንደን)
ሸር በማደርገዎ ልባዊ አድናቆቴ ይድረስልኝ

Image may contain: 1 person
 
Sign in or sign up to post comments.
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular