" የግዜና የዘመን ተወቃሽ ትውልድ እንዳንሆን !! "

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ በምሐበራዊ ሚዲያያዎች ተከታትየው ነበር :: በተለይ በመግለጫቸውም ትኩረት ባደረኩበትን ብቻ ላይ የግል አስተየትን መግለፅ እወዳለሁ ::
" በሀገሪቱ የመጣው ለውጥ ብቸኛ ባለቤት የኢትዮጵያ ህዝብ ስለሆነ ከውጭ የሚገቡ የፖለቲካ ድርጅቶችን የማግለል አካሄድን ሊከተሉ አይገባም " ሲሉ ተናግረዋል።
እውነት ነው :: በዚህ በኩል ፣አብይ ትክክል ናቸው ::
ኢትዮጵያ በልባችን ውስጥ ልዩነትነታችንን አዝላ ተሸክማ ፣የምትኖር በልዩነት አንድነትን የምትሰብክ የብዙሐን ህብር ብሔር አምባ የመቻቻል ሐገር ፣ የህብረት ምስክር ፣የሶስት ሽህ ዘመን የገድላት ክምር የታሪክ ማህደር የሰው ዘር መገኛ ፣ የሥልጣኔ ምንጭ ናት ::
ነገርግን፣ በወቅቱ የጎሳ ሽንሸና ፣መርዘኛ ውጤት ቀስ በቀስ በትውልዱ ውስጥ እንደ ካንሰር ሁኖ ገብቶ ፣ ትልቁን የሐገር ጉዳይ ትተን የእርስ በእርስ ግጭትንና የምሐበራዊ ቀውስ ለማምጣት በትልቁም በትንሹም እየተቆራቆስን የቅዠት ፍልስፍና ጀምረናል ::
በዚህ ምክኒያት አብይ አድስ ነገር አምጥተው ሐገሪቱን ወደ ተሻለ ስርአት ይዘዋት ሊጏዙ የሚችሉ አይመስለኝም ::
አዲስ አቅጣጫ በመቀየስ የፍቅርና የሰለም ታላቅ ሐገር ለመገንባት የሚችሉበትን ጊዜ ሁሉ በእኛ አለመስማማት ውድ ጊዚያቸውን እየተሻማን የተበላሸውን ሲያስተካክሉ የነቀልነውን ሲተክሉ ጀንበር ወጥታ ትጠልቃለች ::
በዚህ ሁለት ቀን እንኳን አዲስ አበባ ላይ የሚደረግውን የመንጋ ፓለቲከኞ ጭፍራዎች ያዙኝ ልቀቁኝ እሪታና ዳንኪራ ልብ ይሰብራል :: የታገለነው አስፓልትና ግንብ ቀለም እየቀባን ልንደባደብ አይደለም :: የሁላችንም ደም አንድ ነው በማለት መተኪ የለላት ህይወታችንን የገበረነው ወደ ነፃነት ተራራ ለመድረስ ነበር ::
በዚህ ምክኒያት አብይ የሰጡት መግለጫ ወቅታውይና ተገቢም ነው :: " ተነጋግሮ መግባባት መተባበር ሲቻል በተናጠል በመፈክር አሸናፊ መሆን አይቻልም " የሚሉት
አብይ በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫቸውም በሰንደቅ አላማም ጉዳይ
የመንግስታቸውን አቋም ግልፅ አድርገው ተናግረዋል ::
" ባንዲራ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገው ከሆነ ተመካከሮበትና ድምጽ ሰጥቶ መቀየር ይቻላል "
ካልሆነ ግን በጉልበት እኔ ባልኩት ብቻ ይሁን የምንል ከሆነ ኢትዮጵያን ማፍረስ ይሆናል ሲሉም አሳስበዋል።
እርግጥ ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነፃነቱና ለሰንደቅ አላማው ቀናኤና ጀግና ለሐገሩ ሲል በጋራ ማንኛውንም መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑ በውጭ አለም ከረጅም ጊዜ ጀምሮ የታወቀ ነው ::
አባቶቻችን በየዘመናቸው የገጠማቸውን ወራሪ ሐይል መክተው ወቅቱ የሚጠይቃቸውን መስዋዕትነት ከፍለው የሚያውለበልቡት አረንጏዴ ቢጫ ቀይ የነፃነት ምልክት ስለነበር በአደራና በውርስ ተረክበነዋል ::
ከዚህ በተጨማሪም የጥቁሮች የነፃነትና የትግል አርማ ሆኖ በተለያዩ የአፍሪካ ሐገሮች አሁን ድሩስ ሰንድቅ አላማቸውን አመሳስለው ያውለበልቡታል ::
ከዚም ባለፈ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በዃላም የአፍሪካ ህብረት ፅፈት ቤት አዲስ አባ ላይ እንዲሆን መወሱኑ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሕዝብና መንግስት ምን ያህል ክብር እንደተሰጣት የሚገልፅ ነው :: 3.2 ሚሊዮን አመት እድሜ ጠገብ የሆነች ሐገር 100 ሚሊዮን የሚደርስ ከ80 በላይ ብሔር ብሔረሰብ የተለያዩ እምነቶች በመፈቃቀድና በመከባበር በጋራ የሚኖሩባት ሐገር ለዘመናት ሲኖሩባት የአፍሪካን አይደለም የአለምን ትኩርተት የሳበች የድንቅነሽ (የሉሲ) ሐገር የፀረ ኮሎኒያሊዝም ድል አድራጊ ሕዝቦች ዛሬ ስንደቅ አላማ ብርቅ ሆኖባቸው ሊያነታርኩና የጠላት መሰቂያ ሲሆኑ መላውን አፍሪካ ማሳዘኑ አይቀሬ ነው :: ይህ ሰንደቅ አላማ ከኢትዮጵያ አልፎ የአፍሪካ የጥቁሮች የትግል አርማ ለመሆን የበቃ ነው ::
የሶስት ቀለማት ህብር የሆነው አረንጏዴ ቢጫ ቀይ ቀለም ሰንደቅ አላማ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሐብት ነው ::
ይህ ሰንደቅ አላማ ማንም እንደፈለገ የሚያውረደው ማንም እንደፈለገ የሚቀይረው ሳይሆን ገና ተከታታይ ትውልድ የሚረከበው ብሔራዊ አርማች ነው ::
ይህ ሰንደቅ አላማ ልክ እንደ አክሱም እንደ.ላሊበላ ብሔራዊ ቅርስች ነው ::
በቅድመ ታሪክና በታሪክ ዘመን የኢትዮጵያ መገለጫ በደምና በአጥንት አብሮ የተሰፋ ነው ::
አባቶቻችን ፀረ ኮሎኒያሊዝምን ሰባብረው ድል ሲመቱ ያውለበልቡት የነበረው የነፃነታቸው ምልክት ነው ::
ይህ ሰንደቅ አላማ ግልፅ የሆነ የራሱ አደራደር ያለው የራሱ ታሪካዊ ትርጉም ከህዝቦቿ ልዩ ልዩ ትርኢት ፣ ጨዋታ ፣ስነቃል ፣የሐይማኖት የእምነት የጋብቻና የሐዘን ባህላዊ እሴትች ጋር የተጣመረ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ በቀስተ ዳመና ምስል በሰማይ ላይ የሚታይ የክርስቶስ ባንድራ ነው ::
ከዚህ አንፃር የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦች መገኛ የሆነች ሐገራችን ኢትዮጵያ የዚህ ብርቅየ የሆነ ሰንደቅ አላማ ባለቤት ናት ::
ወደድንም ጠላንም ብንጠግብም ብንራብም በዚች አብረን በቆምንባት መሬት ላይ ነው የተወለድነው ::
የምንኖረውም በዚችው ኢትዮጵያ በተባለች ሐገር.ላይ ነው ::
ኑሯችን የተመሰረተውም ሆነ የወደፊት ተስፋችንን በዚችው እትብታችን በተቀበረባት መሬት ውስጥ ነው ::
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን አባባል ልዋስና " ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ ነን" : :
ፈለግነውም አልፈለግነውም አፈር ትቢያ የምንሆነው በዚችው መሬት ውስጥ ነው :: አንድነታችን በልደትም በኑሮም በሞትም በህይወታችንም ሆኑ በኑሯችን በማንነታችንም እኛ ሁላችንም የኢትዮጵያ መሬት ነን ;:
ታዲያ እንዳለመታዱል ሆኖ ይህ ትውልድ.የማይደማመጥ የጀግና ጥላቻ ... እስካሁን ድረስ ያለበት ትውልድ ነው :: ታላላቅ የሐገሪቱ መሪዎች የነበሩት በደንቁርና የምናበሻቅጥ ነን ::
እነዚህ ታሪክ የሚያወሳቸውና የሚያከብራቸው መሪዎች ስናነሳ የአመራር ብቃታቸውና የተጎናፀፉት የሞራል ስብዕና ነው እንጅ የምንናገርላቸው በስማቸው ታቦት ተቀርፆ እናምልክባቸው እያልን አይደለም :: ደጋግመን ደጋግመን የምናዎሳቸው የታሪክን አቅጣጫ ለሐገራቸው ጥቅም እንዲስማማ ለአለምም አንድ አይነት ውጤት አምጥተው አበርክተው ስላለፉ ነው :: ለዚህ በዚህ ፅሁፍ ዘርዝሬ የማልጨርሳቸው ጀግኖች በዎቅቱ በሐገሪቱ የመከራ ቀን በጋራ ዋጋ ከፍለውበት አልፈዋል :: በዚያ የፈተና ወቅት ደግሞ ብዙ ጀግኖች በአንድ ግዜ ማግኜት ያስቀና ነብር :: ስለዚህ የግዜና የዘመን ተወቃሽ ትውልድ እንዳንሆን አብረን ልናስብበትየሚገቡ እጅግ በጣም ብዙ ጉዳዮች ስላሉ ሰከን ብለን ልንደማመጥና ልንከባበር ይገባል ::
ለዛሬው ዝግጄት ጨረስኩ በሌላ ዝግጅት እስክንገናኝ ቸር ይግጠመን::
አለባቸው ደሳለኝ አበሻ (ለንደን)

Sign in or sign up to post comments.
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular